አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ከበላይ አብ ሞተርስ ጋር በመሆን ለደንበኞቹ መኪና በብድር እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማኀበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍጽም አብረሃ ከበላይ አብ ሞተርስ ጋር በዛሬዉ ዕለት የተደረገው ስምምነት የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት ትልቅ ፋይዳ ለዉ ብለዋል፡፡

በተደረገው የስራ ስምምነት መሠረት አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማኀበር መስፈርቱን ያሟሉ ተበዳሪዎችን በሚያቀርበው መሠረት በላይ አብ ሞተርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ ተሽከርካሪዎችን ያቀርባል።

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር በዘጠኝ ሺህ ብር መነሻ ካፒታል ጀምሮ አሁን ላይ ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል አድርሷል።

ማህበሩ ላለፋት አስራ አንድ አመታት ከሰባት ሺህ በላይ አባላትን በማቀፍ እንዲሁም ለአራት ሺህ ያህል ሰዎች የብድር አገልግሎት መስጠቱን አስታወቋል፡፡
ተቋሙ እስከ 12 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የብድር አገልግሎት እንደሚሰጥም ሰምተናል፡፡

በቅርቡም አሚጎስ ከኢትዮ ፒካር ጋር ተመሳሳይ ስምምነት ማድረጉ የሚታወስ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ

ሚያዝያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *