በኬንያ የወርቅ ማምረቻ ቦታ ላይ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ አምስት ሰዎች ሞቱ።

በሃገሪቱ ማርሳቢት በተሰኝችው ግዛት በወርቅ ማምረቻ ቦታ ላይ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ቢያንስ አምስት ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የግዛቲቱ ፖሊስ አዛዥ ፓትሪክ ምዋኪዮ “አስከሬኖቹ የተገኙት ከትናንት በስቲያ ከተጀመረው ፍለጋ በኋላ ነው” ሲሉ ሌሎች ሶስት ሰዎች እስካሁን አለመገኘታቸውን ተናግረዋል።

ይህ ማርሳቢት የተሰኝችው ኬኒያ ግዛት ሃገሪቷን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስን አካባቢ ነው፡፡

የኬንያ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ሂሎ አካባቢ የሚገኘው መደበኛ ያልሆነውን ማዕድን ማውጫ እንዲዘጋ በመጋቢት ወር ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር።

ውሳኔው በአካባቢው ማህበረሰቦች መካከል ግጭት በመነሣቱና ለሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተከትሎ ነበር።

ለሳምንታት የዘለቀው ከባድ ዝናብ የማዕድን ቁፋሮ ሥፍራው እንዲንሸራተት ምክንያት ሆኗል ሲሉ የአካባቢው ባለስልጣን ዴቪድ ሳሩኒ ተናግረዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *