በኢትዮጵያ የኩላሊት እጥበት የሚሰጡ አንዳንድ የህክምና ተቋማት ዋጋ በእጅጉ በመጨመሩ ታካሚዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ ነው ተባለ፡፡

ህክምናውን ለማግኘት አንድ የኩላሊት ታማሚ ለአንድ ቀን እጥበት ብቻ በትንሹ 2500 ብር ያወጣል ተብሏል።

የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት አንድ ሰው በወር የመድሀኒት እና የትራስፖርት ወጪን ሳይጨምር ለኩላሊት እጥበት ብቻ በትንሹ እስከ 30 ሺ ብር እንደሚያስፈልገው ገልፀዋል።

ህመምተኛው የትም አይሄድም በሚል እሳቤም አንድ አንድ ሆስፒታሎች ያለአግባብ ጭማሪ እያደረጉ ስለመሆናቸው አንስተዋል።

በዚህ ምክንያት በሳምንት ሶስት ጊዜ ህክምናውን ማግኘት ሲገባቸው በሚደረጉ የዋጋ ጭማሪዎች በሳምንት ሁለት ጊዜ ለመውሰድ እንደተገደድ ተናግረዋል።

ህብረተሰቡም ለችግሩ ትኩረት እየሰጠው እንዳልሆነ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጠዋል፡፡

ማህበረሰቡም ለችግሩ ትኩረት ሰጥቶ በመጀመሪያ እራሱን ከበሽታው እንዲከላከል እና በተለይ የደም ግፊት እና የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች

በተገቢው መልኩ የህክምና ክትትል ማድረግ እንዳለባቸውም አንስተዋል ።
በሽታውንም ለመከላከልም ህብረተሰብ ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ የጤና ምርመራ ማድረግ እንደሚገባው ጠቅሰዋል።

በሐመረ ፍሬው

ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *