በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ለኮንስትራክሽን እና ለተለያዩ አገልግሎቶች ተብለው በተቆፈሩ ጉድጓች ገብተው ለህልፈት የሚዳረጉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡
ይህ ቁጥር በ2016 አመት የተከሰተ እንደሆነ ነው የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያስታወቀው፡፡
በበጀት አመቱ በጠቅላላ 78 ሰዎች በተለያዩ ድንገተኛ አደጋዎች መሞታቸውንም ገልጻል፡፡
የአዲስ አበባ እሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ድንጋይ እና ማእድናት ለማውጣት በሚል የሚቆፋፈሩ ጉርጓዶች ክፍት በመተዋቸው ምክንያት ውሃ እንዲያቁሩ እና ዋና ለመዋኘት የሚገቡ ሰዎች ህይወታቸውን የሚያጡበት ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ በግለሰብም ሆነ በመንግስት ለግንባታ ስራዎች ተብለው ተቆፍረው የሚተዉ ጉድጓዶች እንዳሉም ገልፀው ፤ በዚህም አንዳንዶቹ ስራው ሲካሄድ በቂ ከለላ እና ጉድጓድ ስለመኖሩ ምልክት እንደማይቀመጥና አደጋዎችም እየተበራከቱ መምጣታቸውን ገልፀዋል፡፡
ድንጋይ ለማውጣትም ሆነ ሌሎች ማዕድናትን ለማውጣት ፍቃድ የሚሰጠው አካል አስፈላጊው ክትትል ማድረግ ፣የተቆፈሩ ጉድጓዶች አካባቢ መከለል፣አደጋን ተከላክለው ከሚሰሩ ተቋማት ልምድ መውሰድ ፣ የተቆፈሩ ጉድጓዶችን ተከታትሎ መክደን / መድፈን/ መዝጋት እንደሚገባ መክረዋል፡፡
ህብረተሰቡም የራሱን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ነው የተናገሩት፡፡
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 04 ቀን 2016 ዓ.ም
