ሁከቱ ባሳለፍነው ሰኞ የጀመረ ሲሆን መነሻውም በዋና ከተማዋ ዳካ ውጭ በሳቫር የሚገኘውን የጃንጊርናጋር ዩኒቨርሲቲን ዉስጥ ነዉ ፡፡
በ1971 ሀገሪቱ ከፓኪስታን ነፃ የወጣችበት ጦርነት የተሳተፉ የወታደር ልጆችን ጨምሮ የኮታ ስርዓቱ ከግማሽ በላይ ጥሩ ክፍያ የሚከፈላቸው በመሆኑ ተቃዋሚዎቹ ተማሪዎች በጦርነቱ ውስጥ ለተዋጉ ሰዎች የቤተሰብ አባላት ኮታ እንዲቆም ሲጠይቁ ነበር፡፡
የመንግስትን የስራ ኮታ በመቃወም በወጡ እና በመንግስት ደጋፊዎች መካከል ግጭቱ መፈጠሩን የአይን እማኞች ተናገረዋል።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ከአራት ሳምንታት በኋላ እንደሚወስን የተናገረ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሃሲና ጉዳዩ በከፍተኛው ፍርድ ቤት እጅ ነው ብለዋል።
በጃሃንጊርናጋር ዩኒቨርሲቲ አቅራቢያ በሚገኘው በኤናም ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል ከ50 በላይ ሰዎች በአንድ ሌሊት ታክመዋል ሲሉ የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል።
በቁምነገር አየለ
ሐምሌ 09 ቀን 2016 ዓ.ም
