ለአውቶቢስ ብቻ ተብሎ በተፈቀደ መንገድ ላይ በሚጓዙ ከ250 በላይ መኪኖች ላይ ቅጣት እንደተጣለባቸው በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ምስጋና ፋንታው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
በዚህም በአንድ መኪና ከ200 ብር እስከ 400 ብር ቅጣት እንደሚጣልባቸው ገልጸዋል፡፡
ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው የአላግባብ መንገድን በመጠቀም ፍሰቱንም በማስተጓጎል ቅጣት እንደተጣለባቸውም ሃላፊው ነግረውናል፡፡
ከዚህ ቅጣትም ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ እንደቻሉም አቶ ምስጋናው ፋንታሁን ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
የተቀጡት መኪኖች ከግንቦት ጀምሮ እስከ ሰኔ ባሉት ሁለት ወራት እንደሆነ የነገሩን ሃላፊው በደንብ ቁጥር በ395 መሰረት እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነም ጠቁመዋል።
የቁጥጥር ስራውም ከጠዋት ከ12 ስዐት እስከ 4 ሰዓት እንዲሁም ከማታ 10 ሰዓት እስከ 2 ሰዓት እንደሚደረግ የገለጹልን ኃላፊው፤
ቁጥጥሩ አሁንም እንደሚቀጥል እና አሽከርካሪዎች የወጣውን የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 395 ማክበር ካልቻሉ ቁጥሩ ከዚም ከፍ ሊል እንደሚችል አቶ ምስጋነው ለጣቢያችን ገልጸዋል።
በለአለም አሰፋ
ሐምሌ 09 ቀን 2016 ዓ.ም
