የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ በቅዳሜና እሁድ ገበያ ምርታቸውን ለሚያቀርቡ ነጋዴዎች ምርት እና አገልግሎታቸውን በጥራት እንዲያቀርቡ በማለም የደረጃ አሰጣጥ መከናወኑን ለጣቢያችን ተናግረዋል።
በዚህም በመዲናዋ ዉስጥ ለሚገኙት 193 የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ዉስጥ ለ1 መቶ 72 የሰንበት ገበያ ነጋዴዎች እስታንዳርድ መዉጣታቸዉን ነግረዉናል፡፡
ደረጃው የተሰጣቸው ባላቸው የገበያ ስፋት፣ምርት፣የገዢዎች አያያዥ፣ወጥ በሆነ የአሻሻጥ ስርዓት ፣የምርት አይነት ብዛት እና ስርዓት ነው ብለውናል።
አቶ ሰዉነት አራት ለሚሆኑትን የሰንብት ገበያዎች በሚሰጡት አገልግሎት እና በሚያቀርቡት ምርት መጠን ከደረጃ በታች በመሆኑ ሳይሰጣቸዉ እንደቀረም ተቁመዋል፡፡
ሃላፊዉ በ2011 የሰንበት ገበያ በቁጥር11 ብቻ ነበረያሉ ሲሆን ፤አሁን ላይ ወደ 193 መድረሱን ነግረውናል።
ይህም የሚያሳየው የሰንበት ገበያ ምንያህል ጠቃሚ እንደ ሆነ እና የዜጎች ፍላጎት መጨመሩን ያሳያል ብለዋል።
በተጨማሪም በነዚህ ገበያዎች ወጥ የሆነ አሰራር እንዲኖር ለማስቻል እንዲሁም ማህበረሰቡ ከተማ አስተዳደሩ ባስቀመጠው የወጋ መጠን በላይ ሲጠይቁ ጥቆማ እዲያደርጉ በሰንበት ገበያው ውስጥ ለሚተውኑት ነጋዴዎች ተመሳሳይ ስማቸው እና ስልክ ቁጥራቸው ያለበት ዩኒፎርም መሰጠቱን ነግረውናል።
በልዑል ወልዴ
ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም
