በጉራጌ ዞን  ንፋስ እና በረዶን ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ ከ 38 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል ተባለ፡፡

ባለፈው ሳምንት ሀምሌ 4 ቀን 2016 አ.ም ምሽት 1 ሰአት በጉራጌ ዞን  ንፋስ እና በረዶን ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ  በሰብል ምርት ላይ ጉዳት መድረሱን የወረዳው ግብርና ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ጉዳቱ የደረሰው በጉራጌ ዞን በእኖር ኤነር መገር ወረዳ ሰባት ቀበሌዎች  መሆኑን የወረዳዉ ግብርና ፅህፈት ቤት ሀላፊ መላኩ ሳህሌ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በጣለው በዚህ ከባድ ዝናብ በ6መቶ 14 ነጥብ 95 ሄክታር ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱ  ሀላፊዉ አስታውቀዋል።

ይሄም በገንዘብ ሲተመን 38 ሚሊዮን 6 መቶ 28 ሺህ 6 መቶ 30 ብር የሚገመት ንብረት መሆኑን ነግረውናል፡፡

እስካሁን  ምንም አይነት ድጋፍ ለተጎጂዎች እንዳልተደገ እና በቀጣይ ድጋፍ ለማድረግ ከሚመለከታቸዉ ሌሎች አጋር መስሪያቤቶች ጋር በመሆን ድጋፍ እያሰባሰብን  እንገኛለን  ብለዋል፡፡

ማህበረሰቡም የጉዳቱ ሰላባ ለሆኑ አርሶ አደሮች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ሐምሌ12 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *