በጥርስ ላይ ጉዳት ሲያጋጥም ወዲያውኑ ምን ማድረግ ይገባል?

በንግግር፣ በይቅርታ እንዲሁም በዝምታ ማለፍ የሚችሉ አጋጣሚዎች ስር ሰደው ወደ ግጭት እና ድብድብ ሊያመሩ ይችላል፡፡

የትራፊክ ህግን ባልጠበቀ መንገድ በማሽከርከር ሰዎች ለትራፊክ አደጋ ሲዳረጉም የሚስተዋል ይሆናል።

በድንገተኛ አደጋዎች እና ህፃናት በሚጫወቱት ወቅት ሊወድቁና የመመታት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል።

በጥርስ ላይ የሚደርስ የመሸረፍ፣ የመነቃነቅ እና የመውለቅ ጉዳት በእነዚህ ሁኔታዎች ላይ ከሚደርሱ አደጋዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

አደጋ ሲያጋጥም ሰዎች ድንጋጤ ውስጥ ሰለሚሆኑ በተቻለ አቅም ለመረጋጋት እንዲሞክሩ እና ጉዳት የደረሰበትን ጥረስ በመያዝ ወደ ጤና ተቋማት መሄድ እንደሚገባ የነገሩን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የጥርስ ሀኪም ዶክተር ብሩክ በርይሁን ናቸው፡፡

በተለምዶ የሚስተዋሉ ስህተቶች ምንድን ናቸው?

  • በውሃ ውስጥ ጥርስን ማስቀመጥ
  • በሳሙና እና የኬሚካል ይዘት ባላቸው ማጽጃዎች ጥርስን ለማጽዳት መሞከር
  • ከ30 ደቂቃ በላይ ጥረስን ማስቀመጥ ናቸው።

በጥርስ ላይ ጉዳት ሲያጋጥም ምን ማድረግ ይመከራል?

  • ጉዳት የደረሰበትን ጥር መስታወቱን ወይም ቀለሙ ነጭ የሆነውን ክፍል በመያዝ ከወደቀበት ቦታ ማንሳት
  • በወተት ውስጥ ጉዳት የደረሰበትን ጥርስ ማስቀመጥ
  • የጥረስን ሴል ላለመጉዳት በምንም አይነት ሳሙና መሰል ማጽጃዎች ማጽዳት አይመከርም
  • ጥረስ ንጽናውን በጠበቀ መልኩ ወደ ጤና ተቋማት ለመውሰድ እና አገልግሎት እዲሰጥ ለማድረግ በጥሩሱ ላይ ንጹህ ውሃ ብቻ ማፍሰስ ይመከራል
  • ጥርሱ በተነቀለበት ቦታ ላይ ወይም በጉንጭ መያዝ
  • ከተቻለ በ30 ደቂቃ ውስጥ ወደ ጤና ተቋማት መሄድ እንደሚገባ ተነግሯል፡፡

ጥርስ ከተሸረፈ የጥርሱን ስር ስለሚጎዳ ደም እንዲረጋ እንዲሁም ኢንፌክሽን እና የጥርስ ቀለም መቀየር ከረጅም ጊዜ በኋላ የሚስተዋሉ በመሆኑ የመጥቆር እና ህይወቱን እንዲያጣ ምክንያት ይሆናል ተብሏል፡፡

የጥርስ መሸረፍ በብዝት የሚጠያጋጥም በመሆኑ በጥርስ ላይ ማንኛውም አደጋዎች ሲያጋጥሙ በባለሞያ መታየት እንደሚስልግ ተነግሯል፡፡

በጥርስ ስር የህክምና አገልግሎት ጉዳት የደረሰበት ጥርስ ዳግም አገልግሎት እንደዲሰጥ ማድረግ እንደሚቻል ተነግሯል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *