በትልቁ የሱዳን የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ዉስጥ ረሃብ መከሰቱ ተሰምቷል፡፡

በሱዳን የቀጠለዉ የእርስ በእርስ ጦርነት በዳርፉር በሚገኝ እና 5መቶ ሺህ ስደተኞችን በያዘዉ ካምፕ ዉስጥ ረሃብ መከሰቱን ገለልተኛ የምግብ ደህንነት ባለሙያዎች ማህበር አስታወቀ፡፡

ለ16 ወራት የቀጠለዉ ጦርነት ወደ ስፍራዉ የሚገቡ የምግብ እርዳታዎች ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተከትሎ ይህ ረሃብ ለመከሰት ምክንያት ሆኗል ሲል ማህበሩ ገልጿል፡፡

በፈጥኖ ደራሹ ሃይል እና በአገሪቱ ጦር መካከል የቀጠለዉ ጦርነት የዓለማችን ትልቁ የሰብዓዊ ቀዉስ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በዚህም 10 ሚሊየን ሰዎች ከቤታቸዉ እንዲፈናቀሉ ምክንያት መሆኑም ተገልጿል፡፡

ይህ መረጃ ይፋ የሆነዉ በ2 ሳምንት ጊዜ ዉስጥ በአሜሪካ አሸማጋይነት ንግግር ለማድረግ እየታሰበ ባለበት ወቅት ነዉ፡፡

የፈጥኖ ደራሹ ሃይል ወደ ጄኔቫ ለመሄድ መስማማቱ የተገለጸ ሲሆን፤ የአገሪቱ ጦር ግን ረቡዕ ዕለት በመሪዉ አልቡርሃን ላይ የግድያ ሙከራ መደረጉን ተከትሎ ወደ ስፍራዉ መሄዱ ግልጽ አልሆነም፡፡

እስከዳር ግርማ
ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *