በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡
እስከ አሁን የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ መረጋገጡን እና የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል መገለጹን ወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ያገነነው መረጃ አመላክቷል፡፡
ከክረምቱ ማየል ጋር በተያያዘ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደራሽ ውኃ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ እየተበራከተ በመሆኑ ሕብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም
