አፍታ ሜይራ ግሩፕ የቤት ብድር ጀምሬያለሁ አለ።

ቤቶቹን ለሚዲያ ባለሙያዎችም ይዤ መጥቻለሁ ብሏል።

አፍታ ሜይራ ግሩፕ ከብራይት ብድርና ቁጠባ ጋር በመተባበር የቤት ብድር መጀመሩን አስታውቋል።

ደንበኞች 25 በመቶ ሲቆጥቡ አልያም ሲከፍሉ ቀሪው 75 በመቶ በብራይት ብድርና ቁጠባ የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል።

በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ቆጥበው አልያም አስቀድመው 25 በመቶ መክፈል የሚችሉ ደንበኞችን የቤት ባለቤት አደርጋለሁ ብሏል።

15 ፕሮጀክቶችን ይዘው መምጣታቸውን እና አሁን ላይ ሁለቱ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ መግባታቸውን የገለፁት የአፍታ ሜይራ ግሩፕ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አሚር አብዱልዋሀብ ናቸው።

ደንበኞች ለቤት ሲመዘገቡ ገንዘቡን ለአፍታ ሜይራ ግሩፕ የሚከፍሉት ሳይሆን በብራይት ብድርና ቁጠባ በከፈቱት የግል አካውንታቸው የሚያስቀምጡት መሆኑንም ተናግረዋል።

ግፋ ቢል እስከ 1 ዓመት ከ6 ወር ድረስ ቤቱን እንደሚያስረክብ የገለፁት አቶ አሚር፤ በመጀመሪያው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ግን የቤት ባለቤት መሆን እንደማይቻል ነው ያነሱት።

ቀሪውን ክፍያ ደግሞ እስከ 10 ዓመት ባለው ጊዜ ቤቱን እየኖሩበት የሚከፍሉት ነው ብለዋል።

25 በመቶ ክፍያው እንደየቤቱ መጠን የተለያየ መሆኑም የተነሳ ሲሆን ፤ ቅድሚያ የሚከፍሉ በቅድሚያ ቤታቸውን የሚያገኙ መሆኑን ነው አቶ አሚር የተናገሩት።

75 በመቶ የሚሆነው የብድር መጠን እስከ 10 ዓመት ጊዜ ተከፍሎ የሚያልቅ መሆኑም ተነስቷል።

የወለድ ምጣኔው ለሴቶች እና ለወንዶች የተለያየ ሲሆን፤ ከ14.5 በመቶ እስከ 15.5 በመቶ ድረስ የሚታሰብ ነው።

እነዚህ ፕሮጀክቶች በቦሌ ቡልቡላ፣ ለቡ መብራት፣ ጎፋ መብራት እና መገናኛ አከባቢ የሚሰሩ ናቸው።

በእስከዳር ግርማ

ነሃሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *