የብሩህ ፋይናንሻል ዋና መስራችን ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ገታቸዉ ባሻወረድ መንግስት የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ገበያዉን ምንም እንኳን ለዉጪ ክፍት ያደረገ ቢሆንም በሀገሪቷ አሁን ላይ በዘርፉ የሰለጠኑ ባለሞያዎች እጥረት ፈተና ይሆኑበታል ብለዋል፡፡
አቶ ጌታቸዉ ለዉጪ ባለሃብቶች ለዓመታት ዝግ ተደርጎ የቆየዉን የፋይናንስ ዘርፉን ክፍት መደረጉን ተከትሎ በሀገሪቷ የሚገኙ ተቋማት ከፍተኛ የገበያ ዉድድር ይፈጠራልም ብለዋል ፡፡
በዚህ ምክንያት በገበያዉ በባንኪንግ፤በፋይናስ ፤በኢንሹራንስ እና በካፒታል ገበያ ዘርፍ የሰለጠነ ብቁ ተወዳዳሪ የሚያደርገን ሰራተኛ የለንም ብለዋል፡፡
በተለይ ደግሞ ሀገሪቷ በሰለጠነ የሰዉ ኃይል በበዙ የምትፈተንበት ዘርፍ እንደሆነ የሚነገርለትን የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ በስርዓተ ትምህርት ዉስጥ አለመካተቱ እና ትኩረት አለመሰጠቱ ችግሩን ያገዝፈዋል ብለዋል።
አሁንላይ በዘርፉ ያለውን የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረትን ለመቅረፍ የሚያስችሉና ከአዳዲስ ቴክኖሎጂ ጋር ባለሙያዎችን የሚያስተዋውቁ አለምአቀፍ ስልጠናዎች ለመድን ሰጪ ተቋማት ከ ኢትዮጵያ መድን ሰጪዎች ማህበር ጋር በመሆን ስልጠና እየሰጠን እንገኛለን ብለዋል።
ልዑል ወልዴ
ነሃሴ 2 ቀን 2016 ዓ.ም
