በሀገሪቱ ያሉ በረሃማ አካባቢዎች ለመለየት እና የተተከሉ ችግኞች መልማታቸዉን ለማረጋገጥ የቴክኖሎጂ እጥረት አለ ተባለ።

ባለፉት አምስት አመታት የተተከሉ ችግኞች የተከላ ቦታዎች ምን ያህል እንደሸፈኑ እና የመፅደቅ መጠናቸዉን ለማረጋገጥ የቴክኖሎጂ ክፍተቶች እንዳሉ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ዶ/ር ግዛቸዉ ካቢቴ ለኢትዩ ኤፌም ተናግረዋል።

የተተከሉ ችግኖችን በጂኦ ስፓሻል ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ የመከታተል እና የመቆጣጠር ስራን እየሰራ የሚገኘዉ የስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት በአጭር ጊዜ እና አቅም መረጃዎችን ለመሰብሰብ እንደተሞከረ ገልፀዋል።

ሆኖም እየተሻሻሉ የሚመጡ የመረጃ ጠቋሚ  ቴክኖሎጂ ከመጠቀም አንፃር በቂ እንዳልሆነ እና  መረጃዎች ለመሰብሰብ እንደገደባቸዉ  ለጣቢያችን ተናግረዋል።

ከግዥ ወጪ የሚመጡ የመረጃ ማግኛ መንገዶችን በመጠቀም እየሰሩ እንደሆነ የተናገሩት ዶ/ር ግዛቸዉ አለምአቀፍ የዘርፉ ተቋማት መረጃዎችን በመስጠት ማገዝ አለባቸዉ ብለዋል።

አያይዘውም ቴክኖሎጂዎቹን ለሚያስፈልገዉ የመረጃ ማሰባሰብ ስራ ለመጠቀም በዘርፉ ያለ የተማረ የሰዉ ሀይል እጥረት እንዳለባቸዉ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2030 የደን ሽፋን መጠኗ ሰላሳ በመቶ መድረስ እንዳለበት ተነግሯል።

በቁምነገር አየለ

ነሐሴ 08 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *