“ሲቢኢ ብር ኘላስ ኤክስፖ 2017” በሚል ስያሜ የአዲስ ዓመት መዳረሻ ኤግዚቢሽን እና ባዛር ሊከፈት ቀናቶች ቀርተውታል ተባለ።

ታሜሶል ኮሙኒኬሽን እና ሊያን ቢዝነስ ግሩፕ ከአሴንቲክ ሶሉሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ኤክስፖ ከነሐሴ 15 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ለ21 ተከታታይ ቀናት እንደሚካሄድ ተገልጿል ።

ይህንን ኤክስፖ በዓይነቱ ልዩ የሆነና ደረጃውን የጠበቀ ብሎም ለሻጭ፣ ለጎብኚና ለሸማች ምቹ እንዲሆን ከስነ-ውበታዊ ጉዳዮች ጀምሮ የተለየየ ሥራዎችን በመስራት ሲዘጋጅ መቆየቱንም አዘጋጆቹ ጠቅሰዋል ።

በኤክስፖው ከ400 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ድርጅቶች ይሳተፉበታል ተብሏል።

ከዋነኛው አጋሩ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በፈፀመው የታይትል ስፖንሰርሺፕ ስምምነት “ሲቢኢ ብር ኘላስ ኤክስፖ 2017” በሚል የተሰየመው ኤክስፖ ኤግዚቢሽን እና ባዛር ብቻ ሳይሆን የአዲስ አመት ዋዜማ ላይ የሚከወን እንደመሆኑ ደማቅ ፌስቲቫልንም በውስጡ ያካተተ መሆኑን ሰምተናል።

በኤግዚቢሽኑ ታሜሶል ኮሚኒኬሽንስ የእጣ ጨዋታዎች በማወጋጀቱ ጎብኝዎች ወደ ኤግዚቢሽኑ ሲገቡ በሲቢኢ ብር በኩል በቆረጡት የ100ብር ትኬት አማካኝነት የሚያገኙትን የዕጣ ቁጥር በመጠቀም እንደ እድላቸው ከ5 ሺ እስከ ቤት አውቶሞቢል መኪና ለባለ ዕድለኞች በሽልማትነት መቅረቡ ተነግሯል።

ታሜሶል ኮሙኒኬሽን እና ሊያን ቢዝነስ ግሩፕ ከአሴንቲክ ሶሉሽን ጋር በመተባበር የዘንድሮውን የአንቁጣጣሽ ዋዜማ ኤግዚቢሽንና ባዛር ለማዘጋጀት የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት እንተርፕራይዝ የወጣውን ጨረታ በ62 ሚሊዮን ብር ማሸነፋቸውን አስታውሰው አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት በሚል ደማቅ ኤክስፖ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

በሐመረ ፍሬው
ነሐሴ 09 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *