የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር ( ፒኤፍኤ ) የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የተጨዋቾች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን የተጨዋቾች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።
ጥሩ የውድድር አመት ማሳለፍ የቻለው ፊል ፎደን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጡ ይታወሳል።
ፊል ፎደን በአመቱ ውስጥ ለማንችስተር ሲቲ አስራ ዘጠኝ ግቦችን ሲያስቆጥር ስምንት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
የተጨዋቾች የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋችም ይፋ ትድርጓል።
በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ኮል ፓልመር የተጨዋቾች የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።
ኮል ፓልመር ባለፈው አመት ለቼልሲ ሀያ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አስራ አንድ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
ፓልመር በአመቱ ውስጥ የፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች እንዲሁም የፒኤፍኤ የደጋፊዎች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጡ አይዘነጋም።
በጋዲሳ መገርሳ
