የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከሕዳሴ ግድብ 17 በመቶ የኤሌክትሪክ ሃይል በማመንጨት ለሽያጭ እንዳዋለ አስታውቋል።

በበጀት ዓመቱ ኩባንያው 20 ሺሕ 522 ጊጋ ዋት ሰዓት ሃይል ያመነጨ ሲኾን፣ 96 በመቶው ከውሃ፣ 3 ነጥብ 3 በመቶው ከንፋስ እንዲኹም 0 ነጥብ 2 በመቶው ደሞ ከደረቅ ቆሻሻ ማቃጠል የመነጨ እንደኾነ ኩባንያው ገልጧል።

በበጀት ዓመቱ ከመነጨው ኃይል ጊቤ-3 የሃይል ማመንጫ ጣቢያ የ34 በመቶውን ድርሻ ሲይዝ፣ በለስ የኃይል ማመንጫ ደሞ 9 ነጥብ 6 በመቶ ድርሻ እንደያዙ ተገልጧል።

ኩባንያው ከኃይል ሽያጭ ካገኘው ገቢ ውስጥ ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የቀረበው በድምሩ 20 ቢሊዮን ብር ገቢ የተገኘ ሲኾን፣ ለውጭ ገበያ ከቀረበው የኃይል ሽያጭ በጠቅላላው 140 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል ተብሏል።

ኾኖም ለሱዳን እና ጅቡቲ ከቀረበው ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው ገቢ፣ ከኩባንያው ዕቅድ የ26 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱ ተነግሯል።

ባሁኑ ወቅት 7 ሺሕ 242 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችሉ አምስት የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች በግንባታ ላይ እንደሚገኙም ኩባንያው በአፈጻጸሙ ዙሪያ በሰጠው መግለጫ ላይ ተጠቅሷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *