ኢትዮጵያን በካፍ የሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ሀገራት ማጣሪያ ውድድር የወከለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን ለፍፃሜ ደርሰዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን ከካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ ጋር ያደረገውን የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች መሳይ ተመስገን እና እመቤት አዲሱ አስቆረዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፍፃሜ ጨዋታውን ከሁለት ቀናት በኋላ ሐሙስ ከኬንያው ክለብ ኬንያ ፖሊስ ቡሌትስ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።
የፍፃሜው አሸናፊ የሴካፋ ሀገራትን በመወከል በአፍሪካ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚሳተፍ ይሆናል።
በጋዲሳ መገርሳ
ነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም
