በፔሩ ሊማ የሚካሄደው የዓለም ከ 20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በመክፈቻው ላይ ኢትዮጵያዊያን በጉጉት የሚጠብቁት የሁለቱም ፆታ የ5000 ሜትር ፍፃሜ ጨምሮ የተለያዩ የማጣሪያ ውድድሮች ይከናወናሉ ።
በዚህ መሰረት :-
በ 5000 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ከሌሊቱ 7:25 አትሌት መዲና ኢሳ
አትሌት መቅደስ አለምሸት
በ 5000 ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ወድድር ከሌሊቱ 7:55 አትሌት ንብረት ክንዴ
አትሌት አብዲሳ ፈይሳ
ኢትዮጵያን በመወከል የአገራችንን ሰንደቅ ዓላማ ለማውለብለብ ይፋለማሉ ።
በተጨማሪ የማጣሪያ ውድድሮች ቀጥሎ ሲውሉ:-
በ 800 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ከምሽቱ 2:00 አትሌት ጀነራል ብርሃኑ
በ 800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ከምሽቱ 2:55 አትሌት አስቴር አሬሪ
በ 3000 ሜትር ሴቶች መሰናክል ማጣሪያ:- ከሌሊቱ 6:00
አትሌት ሲምቦ አለማየሁ
አትሌት ፍሬሂወት ገሰሰ
በጋዲሳ መገርሳ
ነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ.ም
