ኢትዮ-ቴሌኮም ለማህበራዊ ጉዳዮች ከ694 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ።

ኢትዮ-ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባላቸው ጉዳዮች ላይ በገንዘብ እና በዓይነት በድምሩ 694 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ኩባንያው ማህበራዊ ፋይዳ ባላቸው ዘርፎች ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ-ቴሌኮም በ2017 ዓ.ም መዳረሻ “በአዲስ ጅማሮ! በአዲስ እይታ! በአዲስ ተስፋ! ወደ አዲስ ዓመት” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያየ መንገድ ማሕበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየሰራ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል፡፡

በመላው አገሪቱ በሚገኙ 930 ትምህርት ቤቶች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 75 ሺህ ተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ ማድረጉንና በዚህም ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን አብራርተዋል።

በትናንትናው እለት በቡራዩ ክፍለ ከተማ ውስጥ ለሚገኝው ለኩ ከታ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የአበበች ጎበና የህፃናት ማሳደጊያን ጨምሮ በበጎ አድራጎት ማዕከላት ላሉ ዜጎችም ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የምገባ መርሃ ግብር እንደሚያካሂድም ጠቅሰዋል።

በእስከዳር ግርማ

ጳጉሜ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *