የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የስራ ሀላፊዎችና የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ክስ ተመሠረተባቸው ።
ክሱን የመሠረቱት የህግ ባለሙያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስን ጨምሮ አምስት ሰዎች ላይ ነው ክሰ ተመስርቷል
ክሶቹሞ ግንቦት 5 እና ሰኔ 4 ኦሎምፒክ ኮሚቴው ህገ ወጥ ጠቅላላ ጉባኤ ማድረጉና የገንዘብ ኦዲት አለማድረግ ላይ ያተኮሩ ሲሆን ጉዳዮም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍትሐ ብሄር ችሎትና በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስተዳደር ችሎት አንደሚታይ ተጠቁሟል።
ከክሱ ይዘት ውስጥ ሰኔ 4 ,2016 ዓ .ም በተከናወነው የኦሎምፒክ ኮሚቴ ምርጫ ላይ አትሌት ሀይሌ ገ/ ስላሴ ፍላጎት ሳይኖረውና በሌለበት ተመራጭ መደረጉ የመተዳደሪያ ደንብንና አሰራርን ሰለመጣሱ ፣ የቶኪዮ ኦሎምፒክ 156 ሚሊዮን ብር ኦዲት አለመደረጉ በዋንኝነት ይገኝበታል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኘው ሻለቃ ሀይሌ ገ / ስላሴ ” በተደጋጋሚ ህግና ስርአት እንዲከበር ስንጠይቅና ስንማፀን ብንቆይም ሰሚ በማጣታችን ጉዳዮን ወደ ፍርድ ቤት ወስደነዋል። ይህን ያደረግነው ማንንም ለመጉዳት ፈልገን አይደለም ። ህግንንና ስረአትን ለማስከበር ነው ” ሲል ተናግሯል ።
በጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ.ም
