አፍሪካን እንዘክር 2017 ከህዳር ወሮ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተባለ።

Africa Celebrates 2024 ወይም “አፍሪካን እንዘክር” 2017 ከህዳር ወሮ ጀምሮ ሌጀንደሪ ጎልድ ሊሚትድና የኢትዮጵያ ዝግጅት አጋር የሆነው ማያ ኢቨንትስ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ፣ዩኤንሲኤ እና ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ፌስቲቫሉ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ዝግጅቱ ”Educate African to fit 21st Century” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተነግሯል።

ይህ ፌስቲቫልም በፈረንጆቹ ከኖቬምበር 6 እስከ 10 በአፍሪካ ህብረት እና በኢሲኤ ለማክበር እንደታቀደም ተገልጿል።

የዚህ ፌስቲቫል ዋና አላማም የአፍሪካን የጥበብ፣ የባህል፣ የኢኖቬሽን፣ የቴክ፣ የንግድ እና ሌሎች የልምድ ልውውጦችን ለማድረግ እንደሆነም ተነግሯል ።

በዓመቱ የአፍሪካ ህብረት መሪ ሃሳብ መሰረት፣ የዘንድሮው የ2024 መሪ ሃሳብ “ለ21ኛው ክፍለ ዘመን ተስማሚ የሆነ አፍሪካዊ ማስተማር፡ በአፍሪካ ባህል፣ ቅርስ፣ ትሬክኖሎጂ እና እና ብልጽግና” እንፍጠር ይከበራል፡፡

በፌስቲቫሉ ምን ያህል ሰው ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ግልፅ መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡት የሁነቱ አዘጋጆች ነገር ግን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአፍሪካ ሀገሮች እንደሚገኙም ሰምተናል።

በለአለም አሰፋ

መስከረም 09 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *