የቬንዙዌላው የፎካካሪ ፓርቲ እጩ ጎንዛሌዝ ፤ማዱሮ ምርጫውን ማሸነፉቸውን እንድቀበል ተገድጃለው አሉ፡፡

የቬንዙዌላው ተቃዋሚ እጩ ኤድመንዶ ጎንዛሌዝ በስፔን ጥገኝነት እንድጠይቅ ከመፈቀዱ በፊት አጨቃጫቂ በነበረው የሀምሌ ወር ምርጫ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ አሸናፊ መሆናቸውን እንድቀበል ጫና ደርሶብኛል ሲሊ ተናግረዋል።

ጎንዛሌዝ ባጋሩት የቪዲዮ መልእክትም በዚህ ወር መጀመሪያ በቬንዙዌላ ዋና ከተማ ካራካስ በሚገኘው የስፔን ኤምባሲ ውስጥ ተደብቄ ሳለ የማዱሮ ረዳቶች ደብዳቤ እንድፈርም አስገድደውኛል ብለዋል።

ነገር ግን የቬንዙዌላ ብሔራዊ ምክር ቤት ኃላፊ እና ቁልፍ የማዱሮ አጋር የሆኑት ጆርጅ ሮድሪጌዝ እንዳሉት ጎንዛሌዝ በፈቃዳቸው ፊርማቸውን እዳሰፈሩ ተናግረዋል ።

የቬንዙዌላ ብሔራዊ ምርጫ ምክር ቤት ሀምሌ 28 ባካሄደው ምርጫ ማዱሮ 52 በመቶ ድምጽ ማግኘታቸውን እና ጎንዛሌዝ ደግሞ 43 በመቶ ድምፅ መግኘታቸውን የ61 ዓመቱ ማዱሮ መናገራቸውን የቢቢሲ መረጃ ያሳያል።

በሐመረ ፍሬው

መስከረም 09 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *