” በሶማሊያ ባልተረጋጋ የደህንነት ሁኔታ ውስጥ በውጭ ሃይላት የሚደረግ የጦር መሣሪያ አቅርቦት በመጨረሻ ሀገሪቷ አሸባሪዎች እጅ ላይ እንድትወድቅ በር ሊከፍት ይችላል ” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሤ ተናግረዋል።
ይህን ያሉት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ግንባታ እና ፖለቲካ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሐፊ ሮዝማሪ ዲካርሎ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።
አምባሳደር ታዬ የሶማሊያ ጉዳይ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ” ኢትዮጵያ ሽብርተኞችን ለመዋጋት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች ” ሲሉ አረጋግጠዋል።
” በሶማሊያ ድህረ የአፍሪካ ህብረት ሽግግር ተልዕኮ በሶማሊያ (አትሚስ) የሚኖረው የኃይል ስምሪት ተገቢውን ጊዜ ወስዶ የተልዕኮዎን የኃላፊነትን ፣ መጠን፣ የፋይናንስ ምንጭ እና ቅንጅት በአግባቡ መሠራት አለበት ” ሲሉ አስረድተዋል።
” ሶማሊያ ባልተረጋጋ የደህንነት ሁኔታ ውስጥ በውጭ ኃይላት የሚደረግላት የጦር መሣሪያ አቅርቦት አሸባሪዎች እጅ ላይ ሊወደቅ ይችላል ” ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።
ሮዝማሪ ዲካርሎ ” በቀጣናው እና ከቀጣናው ባሻገርም ተመድ ከኢትዮጵያ ጋር በሰላም ግንባታ ዙሪያ የሚያደርገውን ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል ” ብለዋል።
መስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም
