በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ሁለት የስደተኛ ጀልባዎች ተገልብጠው ቢያንስ 45 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ብዙ ሰዎች ጠፍተዋል ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ጀልባዎቹ ከመስመጣቸው በፊት 310 ሰዎችን አሳፍረው ከየመን መነሳታቸውን የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) አስታውቋል።
የጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጠባቂ “እስካሁን ድረስ 61 ግለሰቦች የጠፉ ሲሆን የማፈላለጉ ስራም ያለ እረፍት ቀጥሏል” ብለዋል።
ከሰኞ ጀምሮ በአይኦኤም የተደገፈ ትልቅ ፍተሻ እየተካሄደ ሲሆን 115 በህይወት የተረፉ ሰዎችን ማዳኑን የጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጠባቂ ገልፀዋል።
“የጠፉትን ለማግኘት እና የተረፉትን ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ቁርጠኞች ነን” ብሏል ኤጀንሲው በመግለጫው።
ጀልባዎቹ የሰመጡት በጅቡቲ ሰሜናዊ ምዕራብ ሖር አንጋር ክልል አቅራቢያ ካለ የባህር ዳርቻ በ150 ሜትሮች (492 ጫማ) ርቀት ላይ መሆኑን የባህር ዳርቻ ጥበቃው ጨምረው መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በሐመረ ፍሬው
መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም
