የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኢራን በእስራኤል ላይ የሰነዘረችው ጥቃት “የከሸፈ እና ውጤታማ ያልሆነ ” ብለውታል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አገራቸው ለእስራኤል የምትሰጠውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ገልጸው፤ ጥቃቱን “የከሸፈ እና ውጤታማ እንዳልሆነ” ተናግረዋል።

በአካባቢው የሚገኙት የአሜሪካ ኃይሎች “እስራኤልን እንዲረዱ” እና የኢራንን ሚሳኤሎችን እንዲያጨናግፉ ማዘዛቸውን ተዘግቧል፡፡

የፔንታገን ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ የአሜሪካ የባሕር ኃይል ወደ እስራኤል በሚምዘገዘጉ የኢራን ሚሳኤሎች ላይ ወደ 12 የሚጠጉ ጸረ ሚሳኤሎችን መተኮሳቸውን ተናግረዋል።

የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ደግሞ “ይህንን የኢራን ድርጊት” በማውገዝ፤ አሜሪካ “በርካታ” ጸረ ሚሳኤሎችን መተኮሷን አረጋግጠዋል።

በዮርዳኖስ መዲና አማን ላይ የጸረ ሚሳኤል ጣልቃ ገብነት አንደነበር የሚያሳይ ምስል እንደነበር ቢቢሲም አረጋግጧል።

ኢራን በሚያዝያ ወር ባደረሰችው ጥቃት ዮርዳኖስ በርካታ ሚሳኤሎችን መትታ ጥላለች።

የእንግሊዝ ተዋጊ ጄቶች በሚያዝያ ወር እንዳደረጉት ሁሉ ማክሰኞ ዕለትም እስራኤልን በመደገፍ ተሳታፊ ነበሩ።

የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ጆን ሄሌይ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ሳይሰጡ የብሪታንያ ጦር ማክሰኞ ማምሻውን “ተጨማሪ ጉዳት እንዳይከሰት ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩሉንን ሚና ተጫውቷል” ብለዋል።

የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር እንግሊዝ ከእስራኤል ጎን መቆሟን እና “ራስን ለመከላከል መብቷ” ዕውቅና እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

ፈረንሣይ እና ጃፓን ደግሞ የኢራንን ጥቃት በማውገዝ ድምጻቸውን በማሰማት ግጭቱ የበለጠ ተባብሶ እንዳይቀጥል ለሁሉም ወገኖች ጥሪ አቅርበዋል።

የመስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *