እንደ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ መረጃ 106 ትምህርት ቤቶች የተፈናቃዮች መጠልያ ሆነው እንዳሉ የገለፀ ሲሆን፤ ይህን ጨምሮ ሌሎች ችግሮች የትምህርት ሂደቱን እየጎዳ ነው መሆኑንም አሳውቋል፡፡
እንደ የትግራይ ትምህርት ቢሮ መረጃ በዘንድሮው 2017 ዓመተምህረት የትምህርት ዘመን በአጠቃለይ 2 ነጥብ 5 ሚልዮን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ሊገቡ ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ይሁንና እስካሁን ከአንድ ሚልዮን በታች አልያም 40 በመቶ ተማሪ ብቻ መመዝገቡ ዐሳውቋል።
መፈናቀል፣ ለትምህርት ያለ ፍላጎት መውረድ፣ የትምህርት መሰረተ ልማትና ግብአት አቅርቦት እጦት ከሚጠበቁት 60 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታው እንዳይመለሱ እንዳደረጋቸው ተነግሯል።
የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ረዳኢ ገብረእግዚአብሔር እንዳሉት በሁሉም የትምህርት ደረጃ እና የተማሪዎች ዕድሜ በከፍተኛ መጠን የሚስተዋል ወደ ትምህርት አለመመለስ እንዳለ የሚገልፁ ሲሆን ይሁንና ይህ በህፃናት ተማሪዎች ወደ ትምህርት መመለስ መጠን ግን የከፋ መሆኑ ይናገራሉ።
የትግራይ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ረዳኢ ገብረእግዚአብሔር በተማሪዎች ምዝገባ እንደታዘብነው አጠቃላይ የተዘገቡ ተማሪዎች 40 በመቶ ደረሰ ብንልም፣ ከፋፍለን ስናየው እስካሁን የተመዘገቡ ህፃናት ተማሪዎች መጠን ከ20 በመቶ አይዘልም።
ከሚጠበቁ ህፃናት ተማሪዎች መካከል 80 በመቶ ወደ ትምህርት ገበታ አልመጡም። ለትምህርት ያለው ፍላጎት በነበርንበት ጦርነት ምክንያት ተሸርሽሮ ያለበተ ሁኔታ ነው ያለው። ስነልቦናው ለመመለስ ሥራ ይፈልጋል።
ይህ ለማድረግ መንግስት፣ በጎ አድራጊዎች መወጣት ያለባቸው ኃላፊነት እንዳለ ሆኖ አካባቢያዊ መፍትሔ ማበጀት ይገባል የሚል መነሻ ነው ያለው” ብለዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም
