የ 2024 የአፍሪካ ሀገራት የቻን ማጣሪያ ጨዋታዎች ድልድል የሚካሄድበት ቀን ታውቋል።

የማጣሪያ ውድድሩ በሁለት ዙሮች በደርሶ መልስ መርሐ ግብር ኢንደሚካሄድ  ተገልጿል ።

በዚህም መሰረት የማጣሪያ ተጋጣሚዎች ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ በግብፅ ካይሮ በሚደረግ የእጣ ማውጣት ስነስርዓት የሚለዩ ይሆናል።

ኢትዮጵያ በውድድሩ ለመሳተፍ በሁለተኛው ዙር ስትሳተፍ በደርሶ መልስ ካሸነፈች ማለፏን የምታረጋግጥ ይሆናል።

የዘንድሮው የቻን ውድድር በኬንያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ በጋራ ያዘጋጅቷል።

አዘጋጆቹ በቀጥታ ማለፋቸውን ተከትሎ ከሴካፋ ሀገራት አንድ ኮታ የሚጨመር ሲሆን የውድድሩ ተሳታፊ ሀገራት ከ 18 ወደ 19 ከፍ እንደሚደረጉ ታውቋል።

የመጀመሪያ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከጥቅምት 15-17 ባሉት ቀናት እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከጥቅምት 22-24/2017 ባሉት ቀናት ይደረጋል።

የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከ ታህሳስ 11 – 13 እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከታህሳስ 18-20/2017 ባሉት ቀናት ይካሄዳል።

የ 2024 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከጥር 24 እስከ የካቲት 21/2017 ዓ.ም ይካሄዳል።

በጋዲሳ መገርሳ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *