የመቀሌ እና የሽሬ ቅርንጫፎች ከ 4መቶ10 ሚሊየን ብር በላይ ያልከፈሉት ዕዳ አለባቸው ተብሏል።
በበጀት አመቱ በአዲስ አበባ፣ ትግራይ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ኦሮሚያ እና ሌሎች ክልሎች የሚገኙ 20 ከፍተኛ የጤና ተቋማት ብድራቸውን መመለስ አለመቻላቸው ነው የተገለፀው።
ገንዘቡ ባለመሰብሰቡ የጥሬ ገንዘብ ዕጥረት እንዲኖር አድርጓል የተባለ ሲሆን፤ ይህ መሆኑ መደበኛ መድሀኒቶችን እንዳያቀርብ እንዳደረገዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡
ተቋማቱ ዕዳቸው ከአንድ አመት እስከ አምስት አመት ጊዜ የቆየ መሆኑንም ለማወቅ ችለናል፡፡
አገልግሎቱ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በነበረው ግጭት ለሽሬ እና መቀሌ ቅርንጫፎች ከ1 ቢሊየን 1መቶ 35 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የህክምና ግብአቶችን ማሰራጨቱን አስታዉቋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 4መቶ10 ሚሊየን ብር የሚሆን የዱቤ ብድር እንዳልተመለሰ ነው ከአገልግሎቱ ያገኘነዉ መረጃ የሚያመላክተዉ፡፡
ከዛሬ 5 ዓመት በፊት ብድር የወሰዱ ተቋማት አሁን ላይ ገንዘቡን ቢመልሱ እንኳን የብሩ የመግዛት አቅም ከአሁኑ ጋር የሚገናኝ ባለመሆኑ የታቀዱ የመሰረተ ልማት ስራዎች እንዲጓተቱ ሆኗል ነዉ የተባለዉ፡፡
በእስከዳር ግርማ
መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም
