የኢትዮጵያ ከ 20ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ አመሻሽ ከ ዩጋንዳ አቻው ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድሩን ያደርጋል።
ብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታውን በታንዛኒያ አዛም ኮምፕሌክስ ስታዲየም ምሽት 12:00 ሰዓት የሚያደርግ ይሆናል።
ዘጠኝ ሀገራት በሁለት ምድብ ተከፍለው የሚወደዳሩበት ከትናንት ጀምሮ ለቀጣዬቹ አስራ አራት ቀናት የሚከናወነው ይህ ውድድር ሀገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ታንዛንያ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ብሩንዲ ይሳተፉበታል።
ከቀናት በፊት ወደ ስፍራው ያቀናው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም ዛሬ የዩጋንዳ አቻውን በመግጠም ውድድሩን የሚጀምር ሲሆን ከሁለት ቀናት በኋላም በሁለተኛው የምድብ ጨዋታ ደቡብ ሱዳንን እንዲሁም ጥቅምት 1 ላይ ደግሞ ብሩንዲን የሚገጥም ይሆናል።
ውድድሩ አዘጋጅዋ ታንዛንያ ከ ኬንያ በሚያደርጉት ጨዋታ የሚጀምር ሲሆን ወደ ፍፃሜ ያለፉ ሁለት ቡድኖችም ዞኑን ወክለው በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ይወዳደራሉ
በጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም
