በተፃራሪ መግለጫዎች ምክንያት በትግራይ ውስጥ ማንኛውም የፀጥታ ችግር እና ስርዓት አልበኝነት እንዲፈጠር እንደማይፈቅድ የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች አስታውቋል።
የፀጥታ ሃይሉ ባወጣው አጭር መግለጫ ” መስከረም 27 ቀን ጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚመለከቱ ሁለት ተፃራሪ መግለጫዎች መውጣታቸውን ተከትሎ በህዝቡ ውስጥ የመረበሽ ስሜት ተፈጥሯል ” ብለዋል።
” የትግራይን ሰላም እና ደህንነት እናረጋግጣለን ” ያሉት የፀጥታ ኃይሎቹ ” በተፃራሪ መግለጫዎች ምክንያት ስርአት አልበኝነት እንዲፈጠር አንፈቅድም ፤ ችግር ሲፈጠርም በዝምታ አንመለከትም ” ሲሉ አሳውቀዋል።
በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 13 የጊዚያዊ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች በማንሳት በሌሎች 14 የድርጅቱ አባላት እንዲተኩ መወሰኑን ከገለፀ በኋላ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ” የመንግስት ግልበጣ ነው ” ያለው ተግባር የሚያርም ” ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ ” ሲል ማምሻውን አስታውቋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም
