በሰሜኑ ጦርነት በርካታ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ከአልነጃሺ መስኪድ  ተዘርፈዋል ተባለ።

በትግራይ ክልል የሚገኘዉ የአልነጃሺ ታሪካዊና ሀይማኖታዊ መካነ ቅርስ ሶስት አመታት በዘለቀዉ የሰሜኑ ጦርነት  መንፈሳዊ ቁሳቁሶች እንዲሁም በመስጂድ የተቀመጡ የቅርስ ይዘት ያላቸዉ መገልገያዎች መጥፋታቸውን ጣቢያችን ሰምቷል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የክልሉ የቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሀይላይ በየነ አልነጃሺ መስኪድ በጦርነቱ መጠነ ሰፊ ጉዳትን ያስተናገደ ቅርስ ነዉ ብለዋል።

የትግራይ የቱሪዝም ቢሮ በመካነ ቅርሱ በዉስጡ የነበሩ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ላይ ዘረፋ እንደተፈፀመበት ማረጋገጥ መቻሉን ገልፀዋል።

በተጨማሪም በቅርሱ ይዞታ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ሰለባ በመሆኑ ምክንያት አደጋ ላይ ወድቆ እንደነበር ተናግረዋል።

አቶ ሃይላይ እንደገለፁት ከሰሜኑ ጦርነት በፊት እድሳት እና የማስፋፊያ ስራዎች ተደርጎለት የነበረዉ ቅርሱ ባለበት አሁናዊ ሁኔታ በድጋሜ ጥገና ለማድረግ ጥናት መደረጉን አንስተዋል።

ከመስከረም ወር አንስቶ የቅርሱ ጥገና ለማስጀመር ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን የገለፁት አቶ ሀይላል ከሰሞኑ የቅርሱ ጥገና መጀመሩንም  ገልፀዋል።

የአልነጃሺ ቅዱስ መስጂድን መልሶ ለመጠገን ከቱርክ ልማት ኤጀንሲ  ጋር በትብብር ለመስራት መቻሉም ተገልፆል።

የቱርክ መንግሥት በቀድሞ የቅርሱ እድሳት ስራን መከናወኑ የሚታወስ ነዉ።

ቁምነገር  አየለ

ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *