በኢትዮጵያ ከተወለዱ 1 ወር ሳይሞላቸዉ ከ1 መቶሺህ በላይ ጨቅላ ህጻናት ህይወታቸዉን ያጣሉ ተባለ፡፡

ከተወለዱ 28 ቀናት ሳይሞላቸዉ 1መቶ 21ሺህ 7መቶ 33 ጨቅላ ህጻናት ህይወታቸዉን እንደሚያጡ ሰምተናል፡፡

በUSAID- የጨቅላ ህጻናትና ህጻናት ጤና ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ዶክተር ያሬድ ታደሰ፤ለጨቅላ ህጻናቱ ሞት እንደ ምክንያት የተቀመጡ ሶስት ምክንያቶች መኖራቸዉን ይገልጻሉ፡፡

የመጀመሪያዉ ከመወለጃ ቀን ቀድሞ መወለድ፣  በወሊድ ወቅት መታፈንና የጨቅላ ህፃናት ኢንፌክሽን ናቸዉ።

ከማህጸን ከወጡ ባለዉ የመጀመሪያዉ 24 ሰአት ለሞት ተጋላጭ የሚሆኑበት እድል ሰፊ ነዉ የተባለ ሲሆን፤ በቤት ዉስጥ በሚወለዱበት ወቅት ለተለያዩ በሽታዎች ተጋላጭ እንደሚሆኑም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በአመት ዉስጥ ዕድሜያቸዉ ከአምስት  አመት በታች የሆኑ ከ 2 መቶ ሺህ በላይ ህጻናትም በሳንባ ምችና በተቅማጥ ህመም ህይወታቸዉን ያጣሉ ተብሏል፡፡

ጨቅላ ህፃናትን በቤት ዉስጥ እያሉ ጡት በማጥባትና በቂ ምግብ በመስጠት ፤ ለክትባት ወደ  ጤና ተቋማት በሚሄዱበት ጊዜም በቂ ቫይታሚን እንዲያገኙ በማድረግ የጨቅላ ህጻናትን ሞት መቀነስ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ህፃናት እንዲሁም የአፍላ ወጣቶች ጤናን በተመለከተ ከክልል እንዲሁም ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል ።

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *