የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቋርጦት የነበረዉን ከአዲስ አበባ ወደ ላይቤሪያ ርዕሰ ከተማ ሞንሮቪያ የሚያደርገዉን በረራ ሊጀምር ነዉ።
አየር መንገዱ እንዳስታወቀዉ በሳምንት ሶስት ቀን ወደ ሞንሮቪያ የሚያደርገዉን የደርሶ መልስ በረራ በመጪዉ ሳምንት ይጀምራል።
ከአፍሪቃ ግዙፉ አየርመንገድ አዲስ የሚጀምረዉ በረራ የአፍሪቃን የንግድ፣የቱሪዝምና የባሕል ልዉዉጥን ለማሳደግ የሚያደርገዉ አስተዋፅኦ አካል ነዉ።
ዘገቦች እንደጠቆሙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን 270 በረራዎችን ወደ መላዉ ዓለም ያደርጋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም
