ለሀገር ዉስጥ ገበያ የሚያቀርቡት የጨርቃ ጨርቅ አልባሳት የጥራት ጉድለት አለባቸው ተባለ።

ኢንደስትሪዎቹ ለሀገር ዉስጥ የሚያቀርቧቸዉ ምርቶች የሚኖራቸዉ የጥራት ደረጃን ለመጨመር የሚታይባቸዉ እንከን እንዳለባቸው ተነግሯል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ልማት ኢንስቲትዩት ተጠባባቂ ስራ አስፈፃሚ አቶ አላምረዉ አያልነህ ኢንደስትሪዎቹ ለሀገር ዉስጥ የሚያቀርብትን ምርት በጥራት  ለማምራት የግንዛቤ ችግሮች አለባቸዉ ብለዋል።

“በምርቱ ላይ ጥራት መጨመር ወጪን ይጨምራል ” የሚል እሳቤ እንዳለ የሚገልፁት አቶ አላምረዉ ኢንደስትሪዎቹ ለሀገር ዉስጥ እና ለዉጪ ገበያ  ለይቶ የማምረት ችግሮች ስለመታየቱ ተናግረዋል።

ለሀገር ዉስጥ ፍላጎት የተለያዩ የጥራት መስፈርቶችን ሳያሟሉ ለገበያ ምርቶችን ማቅረብ ተፈላጊነትን ለመቀነስ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

በጥራት ማምረት ተጨማሪ ወጪ ያስወጣል የሚሉ አመለካከቶች አምራቾች ጋር ሊኖር አይገባም ያሉት አቶ አላምረዉ 85 በመቶ አሜሪካ መዳረሻ የሚያደረግ የዚህ ዘርፍ የዉጪ ንግድ ገበያ ለሀገር ዉስጥ ተጠቃሚ ጥራትን መጠበቅ ይገባዋል ይላሉ።

በኢንዱስትሪዎቹ ላይ የአቅም ግንባታ እና የክህሎት ክፍተቶች እንዳሉ የተገኙ ግምገማዎች ስለመኖራቸዉ ተነግሯል።

ይህንን ለመፍታት አምራች ኢንደስትሪዎች ሊመሩበት የሚገባ ፖሊሲን ተግባራዊ ለማድረግ ስራዎች መኖራቸውን አቶ አላምረዉ ለጣቢያችን ገልፀዋል።

በሀገሪቱ በአሁን ወቅት ከ395 በላይ ከፍተኛ እና መካከለኛ የጨርቃጨርቅ አምራች ኢንደስትሪዎች ያሉ ሲሆን 238 ያህሉ ሀገራዊ አምራቾች ናቸዉ ተብሏል።

ቁምነገር አየለ

ጥቅምት18 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *