በኢትዮጵያ ያሉ ዝሆኖችን በተለየ በባቢሌ ያሉ የዝሆኖችን ቁጥር እና ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ፤ ጥንቃቄ ለማድረግ ጥናት ሊካሄድ እንደሆነ የአየአካባቢ ደን እና ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ገልጿል።
የባለስልጣኑ ዋና ሀላፊ የሆኑት አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ጥናቱ በዚህ ሳምንት በተቀናጀ መልኩ የሚመለከተው ባለድርሻ አካላት ባሉበት ጥናቱ እንደሚካሄድም ተናግረዋል።
ከጥናቱ በኋላ አሁን ላይ ዝሆኖች ያሉበትን ሁኔታ በተመለከታ ሰፊ መረጃ ማግኘት እንደሚቻል አንስተው ጥናቱ በዚህ ሳምንት
እንደሚጀምር ነግረውናል፡፡
ሃላፊው አያይዘውም በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ሲነሳ የነበረውን ችግር የኢንቨስትመንት ድርጅት ከባቢሌ እንዲወጣ ለባለስልጣኑ መወሰኑን ቢያነሱም ያሉ ችግሮች ግን አሁንም አለመቀረፋቸውን ነግረውናል፡፡
በሶማሊያ እና ኦሮሚያ ክልል ድንበር አዋሳኝ ቦታ ላይ የሚገኘውን የባቢሌን የዝሆኖች መጠለያ ችግር ለመፍታተት አሁንም ጥረቶች መቀጠላቸውን ገልፀዋል።
በባቢሌ የዝሆን መጠለያ በዝሆኖች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በተደረገው ህገወጥ ሰፈራ ዝሆኖች የሚኖሩበትና የሚራቡበት ቦታ በእርሻ፣ በከሰል ምርት፣ በመንገድና መኖሪያ ቤት ግንባታ ደን እየመነመነ በመምጣቱ አሁንም ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑንም ባለስልጣኑ ለጣቢያችን ገልጷል።
ለአለም አሰፋ
ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም
