የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሊከሰሱ ነው

የአትዮጵያ ህዘብ እንባ ጠባቂ ተቋም መቀሌ ቅርንጫፍ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት “ከክልሉ ጎን ለምን ተሳትፎ አላደረጋቸህም” በሚል ከስራቸው ተሰናበተው ለሁለት አመታት የቆዩት የፖሊስ ሰራዊት አባለት ምላሽ ባለማግኘታቸው ጉዳዩን ወደ ህግ እንደሚወስደው አስታውቋል።

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ጸሃዬ እምባዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አንደተናገሩት በሚቀጥሉት “አምስት ቀናት” ከጊዜዓዊ አስተዳደሩ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ ጊዜያዊ አስተዳደሩን ፕሬዝዳንት እንደሚከሱ ተናግረዋል።

የአምስት ቀኑ ማስጠንቀቂያ ከጥቅምት 19 /02 /2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚቆጠር ነግረውናል፡፡

አቶ ጸሃዬ ፕሬዝዳነቱን የምንከሰው “አሰራሩ ስለሚያስገድድ እና ያሉበት የስራ ሃላፊ እሳቸውን የሚመለከት ስለሆነ እንጂ” ሌላ አላማ ኖሮን አይደለም ብለዋል።

በአሰራሩ መሰረት ፕሬዝዳነቱ ለክስ የሚቀርቡት ለትግራይ ክልል አቃቢ ህግ ቢሆንም አቃቢ ህጉ ደግሞ በክልል ጊዜዊ አስተዳደር ስር በመሆኑ ምክንያት አቃቢ ህጉ ሀላፊውን ለመክሰስ ስለማይችሉ ክሱ ለፌድራሉ ጠቅላይ አቃቢ ህግ እንደሆነ ነግረውናል፡፡

ቅርንጫ ጽ/ ቤቱ የፖሊስ ሰራዊት አባለቱ ወደ ስራ እንዲመለሱ ውሳኔያቸውን እንዳሳለፉ የነገሩን አቶ ጸሃዬ ውሳኔው ከተወሰነ 33 ቀናት ቢያስቆጥርም እስካሁን ደረስ ምላሽ ባላመገኘቱ ምክንያት “የአምስት ቀን ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ነው ወደ ክስ ለመግባት ተገደናል” ነው ያሉት።

ለአለም አሰፋ

ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *