የማንችስተር ዩናይትድን ቀጣዩ  አሰልጣኝ    ሩበን አሞሪም!!!

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ከሁለት አመታት በፊት ክለባቸው ስፖርቲንግ ሊስበንን ከ 19ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የሊግ ዋንጫ እንዲያሳካ ረድተዋል።

የባለፈው የውድድር አመት ተጨማሪ የሊግ ዋንጫ ለክለባቸው ማሸነፋቸው በታላላቅ ክለቦች አይን ውስጥ እንዲገቡ አድርጓል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በዘንድሮው የውድድር ዘመን ስፖርቲንግ ሊስበንን እየመሩ ያደረጓቸውን ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች በማሸነፍ በሀያ ሰባት ነጥቦች ሊጉን እየመሩ ይገኛሉ።

በዘንድሮው የውድድር ዘመን ስፖርቲንግ ሊስበን በዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች ሰላሳ ግቦችን በተጋጣሚዎቹ ላይ ሲያስቆጥሩ የተቅጠሩበት ሁለት ግቦች ናቸው።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በ 3-4-3 እንዲሁም 3-4-2-1 የጨዋታ አሰላለፍ እንደሚመርጡ ያላቸው ቁጥራዊ መረጃ ያስረዳል።

አሰልጣኙ ኳስ የሚቆጣጠር ፣ ተለዋዋጭ የማጥቃት ባህሪ ያለው እና ጠንካራ የመከላከል መሰረት ያለው ቡድን በመገንባት እንደሚታወቁ ተገልጿል።

አሰልጣኙ በስፖርቲንግ ሊስበን ቆይታቸው ኑኖ ሜንዴዝ ፣ ኑኔስ ፣ ማኑኤል ኡጋርቴ እና ፓልሂንሀን የመሳሰሉ ባለተሰጥኦ ተጨዋቾችን ማብቃት ችለዋል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በቀጣይ ማንችስተር ዩናይትድን ከተረከቡ ከቡሩኖ ፈርናንዴዝ እና ማኑኤል ኡጋርቴ ጋር ዳግም አብረው የሚሰሩ ይሆናል።

በአውሮፓ ስድስቱ ታላላቅ ሊጎች ያለፈው የውድድር አመት ከተጀመረ ጀምሮ እንደ ስፖርቲንግ ሊዝበን ብዙ ጎሎች ያስቆጠረ አንድም ቡድን የለም  126 ጎሎች !

በተመሳሳይ ካለፈው የውድድር አመት ጀምሮ በስድስቱ ታላላቅ ሊጎች እንደ ስፖርቲንግ ሊዝበን ብዙ ጨዋታ ያሸነፈም ቡድን የለም  38 ጨዋታዎች !

ሩበን አሞሪም በማን ዩናይትድ ታሪክ በእድሜ ትንሹ አሰልጣኝ ነዉ 39  አመት ።

ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 20  ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *