ሚያዚያ 16 እስከ ነሃሴ 19 ድረስ በቆየው የመተግበሪያ ማስተዋወቂያ ወቅት በመተገበሪያው ለተማዘገቡ ደንበኞች ከቤት እድሳት ጀምሮ ፣ የሆቴል ፓኬጅ ፣ ስማርት ስልኮች እንዲሁም የተለያዩ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን በዕጣው ተካቷል።
የዚህ የሽለማት አላማው የፍሊንት ስቶንን ቤተሰቦችን ማበረታት አፕሊኬሽኑን ማከተዋወቅ ነው ተብሏል ።
ዛሬ በሚወጣው የፍሊንት ስቶን ሽልማት ዕጣ ውስጥ በመጀምሪያ ዕጣ የቤት እድሳት የባለ ዕድለኛው ቤት የሴራሚክ ወለል ንጣፍ የመታጠቢያ እና የማብሰያ ወለል ከግድግዳ ጋር የሴራሚክ ንጣፍ ሽልማት አበርክተዋል።
በመጨረሻም ቤት ሁሉም ሰው እቅድ ውስጥ ያለ ነገር በመሆኑ የመጀመሪያውን እጣ እጅግ ተፈላጊ ያደርገዋል ተብሏል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም
