የመጠጥ አምራች ድርጅት ቢጂአይ ኢትዮጵያ፣ በባቱ (ዝዋይ)ከተማ ያስገነባውን “የአባ ገዳ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት” በዛሬው እለት አስመርቆ ለባቱና አከባቢው ማህበረሰብ አስረክቧል።
የ ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄርቬ ሚልሃድ፣ ትምህርት ቤቱን ለማስገንባት ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ብሏል።
ት/ቤቱ ፤ ለመማር ማስተማር አስፈላጊ ቁሳቁሶች የተሟሉላቸው ስምንት የመማሪያ ከፍሎችና ንጽህናቸውን የጠበቁ መፀዳጃ ቤት አለው ብለውናል ።
አቶ ሄርቬ ሚልሃድ፣ትምህርት ቤቱ በጠቅላላ በሁለት ጊዜ ፈረቃ ከ 6 መቶ በላይ ተማሪዎችን የማስተናገድ አቅም አለው ያሉን ሲሆን ከኬጂ ጀምሮ እስከሶስተኛ ክፍል ትምህርት ይሰጣል ነው ያሉት፡፡
የባቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አህመዲን እስማኤል በበኩላቸው በከተማዋ አንዱ ችግር ዛሬ ተፈቷል ያሉ ሲሆን አሁን ብዙ ይጠበቃል ብለዋል።
ሆኖም ይህ ትምህርት ቤት ለከተማዋ ብሎም ለሃገር የትምህርት መሠረተ ልማትን ከማስፋፋት በላይ ቢጂአይ ለማህበረሠቡ የሚያደርገውን ድጋፍ በጉልህ የሚያሳይ ተግባር ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ውጭ ድርጅቱ በአከባቢው አቅመደካማ ለሆኑ ከ500 በላይ ለሆኑ አባወራዎች የጤና መድህን ክፍያን በመሸፈን በማሳከም ላይ ይገኛል ተብሏል ።
ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ ቢራና ወይን ጠጅ ምርት በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም በመሆን በሰባት ፋብሪካዎቹ ቢራና ወይን ጠጅ በማምረት ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የድርሻውን በመወጣት ይገኛል ።
ልኡል ወልዴ
ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም
