ማይክ ታይሰን በጄክ ፖል ተረታ !

የአለማችን የምንጊዜም ታላቁ ቦክሰኛ ማይክል ታይሰን ከ 19ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ ገነነበት የቦክስ ፍልሚያ ተመልሶ በ 31ዓመታት ከሚያንሰው ጄክ ፖል ጋር ተፋልሟል።

በመላው አለም በርካቶች በተመለከቱት ፍልሚያ የ 27ዓመቱ ጄክ ፖል በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ችሏል።

ካደረጋቸው 56 ፕሮፌሽናል የቦክስ ግጥሚያዎች በ 50 ድል የተቀዳጀው ማይክ ታይሰን ዛሬ ሰባተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ወጣቱ ጄክ ፖል በበኩሉ የዛሬውን ጨምሮ ካደረጋቸው 11 ፕሮፌሽናል ግጥሚያዎች በ 10 ድል መቀዳጀት ችሏል።

ማይክ ታይሰን ከፍልምያው በኋላ “ ፖል ጠንካራ ተፋላሚ እንደሆነ አውቅ ነበር በደንብ ተዘጋጅቷል ለማንም ማሳየት ያለብኝ ነገር የለም ባደረኩት ነገር ደስተኛ ነኝ ብሏል።

ጄክ ፖል በበኩሉ “ ከማይክ ጃክሰን ጋር መፋለም ክብር ነው ፤ እንደጠበቅኩት በጣም ከባድ ፍልሚያ ነበር የቻልኩትን ሁሉ አድርጌያለሁ።”በማለት ተናግሯል።

ግጥሚያውን ያሸነፈው ጄክ ፖል የ 40 ሚልዮን ዶላር አሸናፊ ሲሆን ተሸናፊው ማይክ ታይሰን በበኩሉ 20 ሚልዮን ዶላር እንደሚያገኝ ተገልጿል።

ተጠባቂውን የሁለቱ ቦክሰኞች ፍልሚያ 4.9 ሚሊዮን ሰዎች በቀጥታ ስርጭት መመልከት ችለዋል።

ጋዲሳ መገርሳ

ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *