የአክሱም ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገብረ መድህን ፍፁም ብርሀን ለዓመታዊው የአክሱም ጽዮን ማርያም ክብረ በዓል 1 ሚሊዮን የሚጠጉ እንግዶች እንዲሚጠበቁ ተናግረዋል።
የቱሪዝም ፅ/ ቤቱ ለጣቢያችን እንደገለፀው በህዳር 21 በሚከበረው የንግስ በአል ላይ 5 ሚሊዮን ብር ገቢ ይገኛል የሚል ዕቅድ መያዙን ገልጿል።
ቢሮው የከተማውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ከሚደግፉ ነገሮች አንዱ የአክሱም ፂዮን የንግስ በአል እንደሆነ ገልፆ በዚህም የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙም አንስቷል።
ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ ተቀዛቅዞ የነበረውን የከተማዋን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለመመለስ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው።
የአየር መንገዱም እድሳት ትልቅ ግብአት እንደሆነም ተመላክቷል።
ለበኡሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል የከተማ አስተዳደሩ ከከተማው ህዝብ ጋር በመሆኑ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙም አሰምተናል ።
ለአለም አሰፋ
ኀዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም
