በኢትዮጵያ 47 በመቶ የሚሆነው የሃይል መቆራረጥ ችግር የሚከሰተው ከዛፎች ጋር በሚፈጠር ንክኪ ነው፣ በመሆኑም ዛፎችን የማፅዳት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል” – አገልግሎቱ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሀገሪቱ “47 በመቶ የሚሆነው የሃይል መቆራረጥ ችግር የሚከሰተው ከዛፎች ጋር በሚፈጠር ንክኪ መሆኑ አረጋግጫለሁ፣ ለሃይል መቆራረጥ መንስዔ የሆኑ ዛፎችን የማፅዳት ስራ አጠናክሬ እቀጥላለሁ” ሲል አስታወቀ። 

“ዛፎች ሲተከሉ ከኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በሶስት ሜትር መራቅ እንዳለባቸው” መመሪያ ቢኖርም ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም ሲል የገለጸው ተቋሙ “በአብዛኛው አካባቢዎች በመኖሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲሁም ከግቢ ውጭ ለኃይል መቆራረጥና ለአደጋ መንስኤ የሆኑ ዛፎችን ከመሰረተ ልማቱ በእጅጉ ተቀራርበው ይገኛሉ ሲል አመላክቷል።

ተቋሙ ይህን ችግር ለመቅረፍ ብሎም በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን የሃይል መቆራረጥ ችግር ለመቀነስ ለሃይል መቋረጥ መንስዔ የሆኑ ዛፎችን የማፅዳትና የቅድመ-መከላከል ስራ እያከናወነ እንደሚገኝም ጠቁሟል።

በምዕራብ አዲስ አበባ፣ በወልዲያ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በሆሳና ሪጅኖች ስር በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ከ193 ኪሜ በላይ የኤሌክትሪክ መስመር የዛፍ ማፅዳት ስራ አከናውኛለሁ ሲል በማህበራዊ ትስስር የፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *