በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ14ኛ ስምንት መርሐግብሮች
የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ ያደረገውን ጨዋታ 3ለ3 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።
የሊቨርፑልን ግቦች መሐመድ ሳላህ 2x እና ጆንስ ሲያስቆጥር ለኒውካስል አይሳክ ፣ ሻር እና ጎርደን ከመረብ አሳርፈዋል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያደረገውን ተጠባቂ የፕርሚየር ሊግ ጨዋታ 2ለዐ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ዊሊያም ሳሊባ እና ጁሪየን ቲምበር አስቆጥረዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር አመቱ በሊጉ አምስተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።
ማንችስተር ሲቲ ከኖቲንግሃም ያደረገውን ጨዋታ በዴብሮይን ፣ ዶኩ እና ሲልቫ ግቦች 3ለ0 አሸንፏል።
ቼልሲ ከሳዝዝሀምፕተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፈዋል።
የሰማያዊዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ዲሳሲ ፣ ንኩንኩ ፣ ማዱኬ ፣ ፓልመር እና ሳንቾ አስቆጥረዋል።
በሌላ ጨዋታ ኤቨርተን ከዎልቭስ ጋር ጨዋታውን አድርጎ 4ለ0 ማሸነፍ ችሏል።
ማንችስተር ሲቲ ከአንድ ወር በኋላ ወደ አሸናፊነት መመለስ ችሏል።
የሊግ ደረጃቸው
1 ሊቨርፑል :- 35 ነጥብ
2 ቼልሲ :- 28 ነጥብ
3 አርስናል:-28 ነጥብ
4 ማንችስተር ሲቲ :- 26 ነጥብ
11 ማንችስትር ዩናይትድ:- 19 ነጥብ
በጋዲሳ መገርሳ
ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም
