በሶሪያ አይ.ኤስ በድጋሚ እንዳይከሰት መስራት አለብን ሲሉ ብሊንከን አስጠነቀቁ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሶሪያ ውስጥ ያለው የእስላማዊ መንግስት ቡድን ዳግም እንዳያንሰራራ መደረግ አለበት ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በፕሬዚዳንት በሽር አላሳድ መንግስትና ህዝብ ቁጥጥር ስር ያሉ ከተሞችን ለመንጠቅ፤ የእስላማዊ መራሹ አማፅያን  ካለፉት ዓመታት ወዲህ የከፋ ሁከትና ውድመት በሃገሪቱ እያደረሰ መሆኑም ተገልጿል ።

ብሊንከን ከኔቶ ስብሰባ ጉባዬ ጎን ለጎን በብራስልስ ውስጥ እንደተናገሩት “በአሁኑ ጊዜ በሶሪያ ውስጥ ውጥረቱን መቀነስ በጣም ወሳኝ ነው።የንፁሃን ዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥና ምናልባትም ከሁሉም በላይ ደግሞ ወደፊት የሚሄድ  የፖለቲካ ስራአት እንዲኖር ማስቻል ያስፈልጋል ።

ቢለኒከን አክለውም “እኛ  ፍላጎቶች በሶሪያ ውስጥ ዘላቂ ደህንነት እንዲኖር ነው፤በተለይም IS IS መልሶ እንዳይነሳ ማድረግና ተመልሶ እንደማይመጣ ማረጋገጥ ፅኑ ፍላጎት አለን” ሲሉ አብራርተዋል ።

በአሜሪካ የሚመራው ጦር በፈረንጆቹ በ2017 ኢራቅ ውስጥ፤ በ2019 ደግሞ በሶሪያ ያሉንት የእስላማዊ መንግሥት ቡድን ጠራርጎ ማስወጣቱም የሚታወስ ነው።

ሆኖም የጂሃዲስት ተዋጊዎች አሁንም ግዛታቸውን የመቆጣጠር እድል ባይኖራቸውም  በሩቅ በረሃማ አካባቢዎች ይንቀሳቀሳሉ ተብሏል ።

አቶኒዮ ቢሊንከን ፤ጂሃዲስቶችን ለመዋጋት በ2014 በአሜሪካ ጦር የተቋቋመው የአለም አቀፍ ፀረ-አይ.ኤስ ጥምረት አካል 900 የሚጠጉ ወታደሮች በሶሪያ፣ 2,500 የሚሆኑት ደግሞ በኢራቅ ውስጥ ተበትነዋል ብለዋል።

ከዚ ውጭ ” በሶሪያ ውስጥ  አሸባሪዎቹን ለመዋጋት ብዙ  ያሰማራናቸው ታጣቂዎች አሉን ብለዋል ።

ልኡል ወልዴ

ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *