በጤና ሚንስቴር የማህበረሰብ ተሳትፎና የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ዳኘዉ ታደሰ፤17 በመቶ በሃገራችን ከአምስት አመት በታች ህፃናት በሳንባምች ወይንም የኒሞንያ በሽታ ይሞታሉ ብለውናል።
ዋና ሥራ አስፈፃሚው ለዚህ ለኒሞኒያ በሽታ መከሰት የተለያዩ ምክኒያት አለ ያሉ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ በቤት ዉስጥና ከቤት ዉጭ ያሉ የአየር ብክለት ይጠቀሳሉ፡፡
ይሁን እና በቤት ውስጥ እንደ ከሰል፣ኩበትና የእንጨት ጭስ ለእናቶችና ህፃናት ኒሞንያ ተጋላጭነት ምክንያተት መሆኑን ነግረውናል።
ከቤት ውጭ ደግሞ በተለይ በከተማ ውስጥ ከመኪናዎችና ከተለያዩ ተቋማት የሚለቀቁ በካይ ጋዞች፣በየቦታው የሚቃጠል ቆሻ፣ እንዲሁም ህንፃዎች ሲሰሩ የሚለቀቁ ኬሚካሎች ይጠቀሳሉ ብለውናል።
አቶ ዳኘዉ ፤የአየር ብክለትን በመቀነስ 50 በመቶ የሚሆነዉን የኒሞኒያን በሽታ መቀነስ ይቻላል ያሉ ሲሆን ለዚህም የአየር ብክለት ልቀቱን ለመቀነስ መፍትሔ ነዉ ያሉትን አጋርተውናል፡፡
ሆኖም ችግሩን ለመቅረፍ በገጠር አከባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦች ጭስ አልባ ምድጃዎችን ሰርተው መጠቀም፣መኖሪያ ቤትን ከኩሽናው መለየትና ኩሽናቸው ከጭስ ነፃ መሆን ይኖርበታል ነው ያሉን።
በከተሞች ያለውን የአየር ብክለትን ለመቀነስ ደግሞ እፅዋትን መትከል፣ሳይክሎችን መጠቀም፣በእግር መንቀሳቀስ እንዲሁም 40 በመቶውን የአየር ብክለቱን ለመቀነስ የህዝብ ትራንስፖረትን ማበራከት ይገባል ተብሏል።
ልኡል ወልዴ
ኀዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም
