በህገወጦች ምክንያት ከስራ ወጥተው የነበሩ ነጋዴዎች ወደ ስራ መመለሳቸዉ ተነገረ

በህገወጦች ምክንያት ከስራ ወጥተው የነበሩ ነጋዴዎች በተሰሩ ስራዎች ወደ ንግድ ስርአቱ   መመለሳቸውን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታቋል።

ግብይቶችን   በደረሰኝ እንዲከውኑ ለማደረግ በተሰራ ስራ  በህገወጦች ምክንያት ከስራ ወጥተው የነበሩ ነጋዴዎች ወደ ንግድ ሰረአቱ  መመለሳቸውን ቢሮው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጿል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የ ኮሙኒኬሽን    ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ  ለጣቢያችን እነደተናገሩት በመርካቶ እና አካባቢው የንግድ እና የግብይት ስርአቱ በህጋዊ መንገድ ለማስኬድ የክትትል እና የቁጥጥር ሰራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።

በከተማው ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ የሚመራ ግብረ ሀይል በማቐቐም ገቢዎች ቢሮ ፤ ንግድ ቢሮ ፤ ሰላምና ፀጥታ እንዲሁም ፍትህ ቢሮን በማቀናጀት እየተሰራ መሆኑን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ተናግረዋል ።

በከተማው ከ 6 ሺህ በላይ ነጋዴዎች የተገኙበት ከተማ አቀፍ  የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መካሄዱንም አስታውሰዋል ።

አቤል እስጢፋኖስ

ታኅሣሥ 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *