ብሄራዊ የጥራት ፖሊሲን ማፅደቅ ጥራትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ስርአት እንዲኖር ያደርጋል ተባለ።

ይህ የጥራት ፖሊሲ  የሚመረቱ ምርቶች ለኅብረተሰቡ እንዲውሉ የሚያስችል እና ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ተወዳዳሪ የሚያደርግ ሁኔታን የሚፈጥር ነዉ ተብሏል።

የብሄራዊ ጥራት ፖሊሲ ረቂቅ መዘጋጀቱን ከዚህ ቀደም ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር መግለፁ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጀት የገበያ ልማት እና የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተክኢ ብርሃን ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ “ይህ የጥራት ፖሊሲ መኖር ማንኛውም አገልግሎት ሰጪ ÷ ላኪ እና አስመጪ በአንድ ቋንቋ መናገር የሚያስችለዉ ህግ ነዉ” ብለዋል።

የዚህ ፖሊሲ መፅደቅ ከአለምአቀፍ ገበያ እና የኢኮኖሚ ማእቀፎች ጋር ለመጣጣም የጥራት  ፖሊሲዉ  ወሳኝነት ሚናዉ የጎላ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።

የግብይት መስፈርቶች የአለም አቀፍ አሰራር ስርአቶች በማካተት የተዘጋጀዉ ፖሊሲ እንደሆነም የኮምኒኬሽን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በዚህም ብሄራዊ የጥራት ፖሊሲን ማፅደቅ ጥራትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ስርአት እንዲኖር የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል

ዳይሬክተሩ አያይዘዉም ምርትን፣ አገልግሎትን ወይም የሥራ አመራር ሥርዓትን የሚመለከቱ ደረጃዎችና ሕጋዊ መስፈርቶች መሟላታቸውን የማረጋገጥ ሃላፊነት ያለዉ የተስማሚነት ምዘና በአለም ንግድ ዉስጥ  ተቀባይነት እንዲኖር እየሰራ ነዉ ብለዋል

ተቋሙ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 6,823 የአገልግሎት ጥያቄዎችን በማስተናገድ የጥራት ማረጋገጥ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልፆል።

ቁምነገር አየለ

ታኅሣሥ 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *