የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮምሽን በቀጣይ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል የተሳታፊና አጀንዳ ልየታ እንደሚያደረግ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት የዘገየውን የምክክር ተሳታፊዎች ልየታ በቀጣይ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።
ኮሚሽነሩ አዝማሚያው ለምክክር መድረክ የማይጋብዝ ከሆነም ከሌሎች ክልሎች ባገኘነው ልምድ መሰረት እንደተደረገው ተሳታፊዎችን ወደ ሌሎች ቦታዎች ወስደን የምንወያይ ይሆናል ሲሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለተከታታይ ስድስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ በስኬት ማጠናቀቃቸውንም ኮሚሺነሩ አንስተዋል፡፡
በዚህም በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ ከ8ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይገኙበታል የተባለው ሀገራዊ ምክክር ከነገ ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሥምንት ቀናት ይካሄዳል ተብሏል።
ተሳታፊዎች ወደ ምክክር ስፍራው እየገቡ መሆኑን ጣቢያችን ከቦታው ሆኖ ተመልክቷል።
ልዑል ወልዴ
ታኀሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም
