ናሽናል ፋይናንስ አከዳሚ፤ በፋይናንሱ ዘርፉ በተለይም በኢንሹራንስ ኢንዳስትሪ የአጭርና ረጅም ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተገልጿል።
ናሽናል ፋይናንስ አከዳሚ በዚህ ዘርፍ እውቅና በማግኘትም የመጀመሪያውና ብቸኛው ተቋምም ሆኗል።
አካዳሚው የተቋቋመውም የፋይናነሱን ሴክተር የሰው ሃብት ፍላጎት ለመሙላት ልዩ ትኩረት እድርጎ የሚሰራ ከፍተኛ ትምህርት ተቋምም ሆነ የስልጠና ተቋም ባለመኖሩ ነው ሲሉም የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር መሰሉ አለሜ ተናግረዋል።

በመሆኑም ይህንን ክፍተት መሰረታዊ በሆነ መልኩ ለመሙላት የሚያስችል በኢንሹራንስ ዘርፍ የረጅም ጊዜ ስለጠና ማለትም “Professional Diploma in Insurance” ለመሰጠት የሚያስችል እውቅና አግኝቶ ስልጠና ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
ለዚህ ስልጠና ማንኛውም የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው ሰው መሳተፍ እንደሚችልም ተነስቷል።
ይሀም ናሽናል ፋይናንስ አከዳሚን በኢንሹራንስኢንዳስትሪ የአጭርና ረጅም ስለጠና ለመስጠት እውቅና ያገኘ የመጀመሪያውና ብቸኛው ተቋም ያደርገዋል።
ተቋም በኢንሹራንስ ዘርፍ አሁን ላይ ማሰልጠን ቢጀምር በቅርቡ ደግሞ በባንክ እና በማይክሮ ፋይናንስ ዘርፍ ማሰልጠን እንደሚጀምሩም ነግረውናል።
ለዓለም አሰፋ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017
